ኮንሴንት ምንድን ነው?

ኮንሴንት ምንድን ነው?

ኮንሴንት = ፈቀደ፣ ተስማማ፣ እሺ አለ - ማለት ነው። (አቢሲኒካ መዝገበ ቃላት)

https://dictionary.abyssinica.com/consent

ኮንሴንት (Consent) በዓለም-አቀፍ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ደንቦችና ሕግጋት ላይ የተመሠረት ደንብና ልማድ ሲሆን ማንም ሰው አካሉን/ አከላቱን አስመልክቶ በሕይወቱ፣ በጤናው፣ በወሲባዊ ግንኙነቱና ሌሎችም ከአካል ጋር በተያያዙ ሁኔታዎች ዙሪያ ራሱ በራሱ የመወሰን ሙሉ ነጻነት እንዳለው ያመለክታል።  በዚህ ጽሑፍ ውስጥ 'ፈቃደኝነት' ተብሎ ተተርጉሟል።

ኮንሴንት ሲተነተን (FRIES በሚሉት ፊዳሎች እንደሚጀምር ያስተውሉ)

F- Freely Given = በፈቃደኝነት የሚሰጥ - ማለትም ያለ ምንም ግፊት፣ ማስፈራራትና ማስገደድ (no pressure, threats or manipulation)

R - Reversible = በማንኛውም ጊዜ ሃሳብን መቀየር የሚያስችል (anyone can change their mind at any time)

I – Informed = ስለ ምን እንደሆነ የሚገልጽ - ማለትም የተስማማንባቸው ነጥቦች/ሀሳቦች/ሁኔታዎች/ተግባሮች የትኛዎቹ ናቸው (you know what you’re agreeing to)

E - Enthusiastic =  ግልጽ ስሜትንና ጉጉትን ወይም ፍላጎትን ያዘለ አዎንታን ያከለ (clear and enthusiastic – not silence, not “I guess” or “maybe”)

S – Specific = አንድ ነጥብ/ጉድይ ላይ ብቻ ያተኮረ - ማለትም ለአንድ ሁኔታ እሺ ማለት ለሁሉም ነገር እሺ ተባለ ማለት አይደለም (saying yes to one thing doesn’t mean yes to everything)

በአብዛኛዎቹ እንደ ካናዳ ያሉ ሀገራት ሕጎች መሠረት በኮንሴንት ወይም በፈቃደኝነት ላይ ያልተመሠረተ ወሲባዊ ግንኙነት ሕገወጥ ነው። በትዳር ውስጥም ይሁን ከትዳር ውጪ ሕጉ ሁሉንም ያጠቃልላል። አንድ ሰው “አልፈልግም ትዉኝ” ካለ እንዲሁም በግልጽ “እሺ እፈልጋለሁ” ብሎ ካልተስማማ ወሲባዊ ግንኙነትን መጀመርም ሆነ ከተጀመረም በኋላ መቀጠል በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው።

በካናዳ ውስጥ ኮንሴንት/'ፈቃደኝነት' በሰፊው የሚተገበር መልካም ባሕል ከመሆኑም በላይ ሰብዓዊ  ክብርንና ደህንነትን ማስጠበቂያ ልምድም ጭምር ነው።

በአንዳንድ ባሕሎች እምቢታ እንደ ነውር ሊቆጠር ስለሚችል አንዳንዶቻችን በአንደበታችን “እሺ” ብለን እየተናገርን በሁኔታችንና በአካላችን የመራቅ/የመሸሽ ወይም በድን የመሆን ባሕርይ በማሳየት አለዚያም አንገታችንን እና ዓይኖቻችንን ዞር በማድረግ እምቢተኝነታችንን እንገልጻለን። የዚህ ዓይነቱ ስውር አገላለጽ በቂ ሆኖ ሊወሰድ ይገባል። አንድ ሰው የማመንታት ወይም እንዳልፈለገ የሚገልጽ/የሚያመለክት ሁኔታን ካሳየ ኮንሴንት አልሰጠም ወይም አልፈቀደም ማለት ነው።

ይልቁንም የወንድ ጾታ ከሆኑ፣ በዕድሜዎ ልቀው ከተገኙ/ከበለጡ፣ በሀብት፣ በሃላፊነት ደረጃና በስልጣን ከፍ ያሉ ከሆኑ የሌሎችን ኮንሴንት ወይም ፈቃደኝነት በግልጽ እንዲሹና እንዲጠይቁ አጥብቆ ይመከራል።

ለምሳሌ፦

  • "አንዴ ጉንጭህን/ ጉንጭሽን መንካት ትፈቅድልኛለህ/ትፈቅጂልኛለሽ ወይ?"
  • "እዚህ ጋ ብስምህ/ ብስምሽ ፈቃደኛ ነህ/ነሽ ወይ?"
  • "ተስማምተን የምናደርገው ቢሆንም በመሃል ሀሳብህን ከቀየርክ ንገረኝ/ ሀሳብሽን ከቀየርሽ ንገሪኝ፤ ያለምንም ጥያቄ እናቆማለን።
  • "_____ ትፈልጋለህ/ ትፈልጊያለሽ ወይ?"
  • ወዘተ

ዝምታ እሺታ አይደለም። በግልጽ በመጠየቅ እዎንታንና ፈቃደኝነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ሰው ሳይፈልግ፣ ሳይስማማና ሳይፈቅድ መንካት፣ መጎንተል፣ ማቀፍ፣ መሳም፣ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት እንዲያደርግ ማስገደድ ስህተትና አለአግባብ ብቻ ሳይሆን ሕገወጥ ተግባርም ስለሆነ ፈቃደኝነትን ወይም ኮንሴንትን አስቀድመን መጠይቅ ባሕላችን እናድርግ።

Read more

አዎን! ወንዶችም ያርጣሉ!

አዎን! ወንዶችም ያርጣሉ!

የሴቶች እርጣት (menopause - ሜኖፖዝ) በእያንዳንዷ ሴት የሕይወት ሂደት ውስጥ በድንገት የሚከሰት ከኤስትሮጀንና ፕሮጀስትሮን የሴቶች ሆርሞኖች መጠን ማሽቆልቆል ሲሆን ከወር-አበባ ማብቃትና የሴቶች የመውለድ ችሎታ ፍጻሜ ጋር የተቆራኘ ሁኔታ ነው። በአንጻሩ ግን የወንዶች እርጣት (andropause - አንድሮፖዝ) በአንዳንድ ወንዶች ዘንድ ብቻ የሚከሰትና ከቴስቶስትሮን የወንዶች ሆርሞን መጠን መቀነስ ጋር የተጣመረ፣ አመጣጡ ደግሞ

By TW
ኦቲዝም - ክፍል ፩

ኦቲዝም - ክፍል ፩

የኦቲዝም ቁጥር መጨመር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. መጀመሪያ ከአንድ መቶ ሃምሳ ልጆች መሀከል አንድ (150፡1) ኦቲስቲክ ልጅ ይገኝ እንደነበረና ከሃያ ዓመታት በኋላ ይህ ቁጥር በሶስት እጥፍ ያህል ጨምሮ በ2020 ዓ.ም. ከሰላሳ ስድስት ልጆች መሀል አንድ (36፡1) ኦቲስቲክ ልጅ መገኘቱን መረጃዎች ያሳያሉ። የኦቲዝም ቁጥር መጨመር ምክንያቱ

By TW
የኮንሸስ ፓረንቲንግ  ፍልስፍና                                              - አስተዳደግ ክፍል ፫

የኮንሸስ ፓረንቲንግ ፍልስፍና - አስተዳደግ ክፍል ፫

ኮንሸስ ፓረንቲንግ (conscious parenting = የንቁ-ሕሊና የአስተዳደግ ዘዴ) በአስተውሎት ወይም በmindfulness ላይ የተመሠረተ የልጆች አስተዳደግ ፍልስፍና ሲሆን የሚከተሉትን ዋና-ዋና ባህርያት ያካትታል። * ወላጆች ስለእራሳቸው የተሻለ ግንዛቤ (self-awareness) እንዲኖራቸው እንዲሁም 'እውነተኛ ማንነታቸውን' (authentic self) በበለጠ ለመረዳት ሲሉ ለስሜቶቻቸው ትኩረት እየሰጡ እራሳቸውን ይመረምራሉ (self-reflection) * የልጆችን አስግተዳደግ አስመልክቶ ያሏቸውን ቅድመ-ግንዛቤዎች በመመርመር አመለካከቶቻቸውንና ተግባሮቻቸውን

By TW
የአንጀት ደህንነት-ለጠቅላላ ጤንነት

የአንጀት ደህንነት-ለጠቅላላ ጤንነት

በአዕላፋት የሚቆጠሩ የተፈላጊ ረቂቃን ነፍሳት ሕብረተሰብ ወይም ማይክሮባዮም (microbiome) በቆዳችን ላይና በሰውነታችን ውስጥ ይገኛል። ከሌሎቹ የሰውነታችን ክፍሎች ጋር ሲነጻጸር በአንጀታችን ውስጥ የሚገኘው የማይክሮባዮም መጠን ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል። የአንጀት ውስጥ ማይክሮባዮም ማይክሮባዮም እንደ ባክቴሪያ (የbacteria ነጠላ ስም ባክቴሪየም- bacterium ነው)፣ ቫይረሶች (virus/ viruses)፣ ፈንገሶችና (fungus/fungi) ጥገኛ ነፍሳት (parasites) ያሉ ተህዋሳትን

By TW