Latest

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፪

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፪

የቤተሰብ መነጣጠል (Disconnection - ዲስኮኔክሽን) በክፍል አንድ የቤተሰብ አባላት በመሀከላቸው በሚኖረው የእርስ በእርስ ጠንካራ መተሳሰር፣ መተባበርና መረዳዳት ላይ ብቻ በማተኮር ለየግል ስሜቶቻቸው ተገቢውን ቦታና ትኩረት ሳይሰጡ በሚቀሩበት ጊዜ፣ እንዲሁም አንዳቸው የሌላኛቸውን ስሜት እንደ የእራሳቸው አድርገው በሚወስዱበት ወቅት መጠማመር ወይም ኢንሜሽመንት ሊከሰት እንደሚችል ለመረዳት ችለናል። አሁን ደግሞ የመነጣጠልን ባህርይ የሚያንጸባርቁ የቤተሰብ አባላት

By TW
የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፩

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፩

በ1960ዎቹ (እ.አ.አ.) የቤተሰብ አወቃቀርንና የአባላቱን ግንኙነቶች አስመልክተው ጥናታዊ ሥራዎችን ያበረከቱ ሰው (Salvador Minuchin) የቤተሰብ አባላትን ገደብየለሽ ስሜታዊ የእርስ በእርስ መጠማመር ኢንሜሽመንት (Enmeshment) ብለው ሰይመውታል። በሌላ አነጋገር በቤተሰብ አባላት መሀከል ያለው የቅርበት መጠንና እራስን በእራስ መግዛትና እራስን መቻል ሚዛኑን ካልጠበቅ መጠማመር ሊከሰት ይችላል ማለት ይቻላል። በቤተሰብ አባላት መሀከል ጤናማ

By TW
የግል ገደቦች - Boundaries

የግል ገደቦች - Boundaries

ከሰዎች ጋር በሚኖሩን ግንኙነቶችና መስተጋብሮች ለእራሳችን ገደቦችን (boundaries - ባውንድሪዝ) ማበጀታችን ለህልውናችን መጠበቅና ለሰላማችን አስፈላጊ ሁኔታ ነው። እራስን መገደብ ከ- ለእራስ ገደብን ማበጀት ለየት ይላል።እራስን መገደብ ስሜትን ከመቆጣጠር ጋር የተዛመደ ነው። በአንጻሩ ግን ለእራስ ገደብን ማበጀት ደግሞ በእሤቶቻችን ላይ የተመሠረተ ሲሆን እራስን ከመገንዘብ ጋር የተሳሠረና ለእራሳችን ምን እንደምፈቅድ ወይም እንደማንፈቅድ

By TW
ሳይጠሩሽ አቤት፣ ሳይልኩስሽ ወዴት!

ሳይጠሩሽ አቤት፣ ሳይልኩስሽ ወዴት!

ሰዎች ሳይጠየቁ ምክርን ለሰው የሚለግሱት መልካም በማሰብ ወይም ተመካሪውን ለመደገፍ ቢሆንም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን የሚችልባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች እንዳሉ ማስተዋል ይገባል። የሚከተሉትን አባባሎች እንደ ምሳሌ እንመልከት፦ * "ጸጉርህ ሳሳ - መመልጥ ጀመርክ እንዴ?!" "ታስሮ የተቀለበ በሬ አከልሽ አይደል እንዴ?!" ወዘተ በማለት መልክና አለባበስን እንዲሁም ሰውነትንና ገጽታን አስመልክቶ ተገቢ

By TW
አራቱ የግንኙነቶች ዕንቅፋቶች

አራቱ የግንኙነቶች ዕንቅፋቶች

ተፈላልገውና ተመራርጠው አብረው ለመሆን ወይም ኑሮን አብረው ለመመሥረት የሚወስኑ ሁለት ሰዎች ወይም ጥንዶች (couples - ካፕልስ) ለግንኙነታቸው መሳካት ወይም አለመሳካት የየግላቸው የሕይወት ልምዶችና ተሞክሮዎች፣ እሤቶቻቸው እንዲሁም ሕልማቸውና ስለወደፊቱ ሕይወታቸው ያላቸው ተስፋ ወሳኝነት አላቸው። ጆን እና ጁሊ ጎትማን የተባሉ ሁለት ሳይኮሎጂስቶች (Drs. John & Julie Gottman) የጎትማን ሜተድ በመባል የሚታወቀውን የጥንዶች ሥነ-

By TW
ኦቲዝም ክፍል ፪-ሥውር  ኦቲዝም

ኦቲዝም ክፍል ፪-ሥውር ኦቲዝም

ኦቲዝም የሚለውን ቃል ስንሰማ ምናልባት በአዕምሯችን ውስጥ የሚቀረጸው በሕፃናትና በልጆች የተመሰለ ምስል ሊሆን ይችላል። ይሁንና በተለምዶ በልጆችና በጎልማሶች ዘንድ ከምናየው፤ ከተነገረን፤ ካነበብነው፤ ከምናውቀው በተለየ መልኩ ኦቲዝም በዓዋቂነት የዕድሜም ጭምር ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገኝ እንደሚችል ማስተዋል ይገባል። ኦቲዝም እ.አ.አ. ከ1911 ዓ.ም. ጀምሮ የሚታወቅ ሁኔታ ሲሆን ለበርካታ አሥርተ-ዓመታት የነበረን

By TW
የልጆችና የወጣቶች የአዕምሮ ጤና - አስተዳደግ ክፍል ፬

የልጆችና የወጣቶች የአዕምሮ ጤና - አስተዳደግ ክፍል ፬

የልጆችና የወጣቶች የአዕምሮ ጤና መዛባት ተስፋፍቶ የሚገኝ ክስተት ከመሆኑም በላይ እንደ የልጆች ጭንቀትና ድባቴ ያሉ ሁኔታዎች የዕድሜ-ልክ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ በመረጃ የተደገፉ ጥናቶች ያሳያሉ። (ከሲ.ዲ.ሲ. የተገኘ መረጃ ) የልጆች የአዕምሮ ጤንነት የልጆች የአዕምሮ ጤንነት የተጠበቀ ነው ብለን ስንል የአዕምሮ ጤና መዛባት እንደሌላቸው በማረጋገጥ መመስከርን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ጤንነታቸው

By TW
አዎን! ወንዶችም ያርጣሉ!

አዎን! ወንዶችም ያርጣሉ!

የሴቶች እርጣት (menopause - ሜኖፖዝ) በእያንዳንዷ ሴት የሕይወት ሂደት ውስጥ በድንገት የሚከሰት ከኤስትሮጀንና ፕሮጀስትሮን የሴቶች ሆርሞኖች መጠን ማሽቆልቆል ሲሆን ከወር-አበባ ማብቃትና የሴቶች የመውለድ ችሎታ ፍጻሜ ጋር የተቆራኘ ሁኔታ ነው። በአንጻሩ ግን የወንዶች እርጣት (andropause - አንድሮፖዝ) በአንዳንድ ወንዶች ዘንድ ብቻ የሚከሰትና ከቴስቶስትሮን የወንዶች ሆርሞን መጠን መቀነስ ጋር የተጣመረ፣ አመጣጡ ደግሞ ቀስ-

By TW
ኦቲዝም - ክፍል ፩

ኦቲዝም - ክፍል ፩

የኦቲዝም ቁጥር መጨመር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም. መጀመሪያ ከአንድ መቶ ሃምሳ ልጆች መሀከል አንድ (150፡1) ኦቲስቲክ ልጅ ይገኝ እንደነበረና ከሃያ ዓመታት በኋላ ይህ ቁጥር በሶስት እጥፍ ያህል ጨምሮ በ2020 ዓ.ም. ከሰላሳ ስድስት ልጆች መሀል አንድ (36፡1) ኦቲስቲክ ልጅ መገኘቱን መረጃዎች ያሳያሉ። የኦቲዝም ቁጥር መጨመር ምክንያቱ

By TW
የኮንሸስ ፓረንቲንግ  ፍልስፍና                                              - አስተዳደግ ክፍል ፫

የኮንሸስ ፓረንቲንግ ፍልስፍና - አስተዳደግ ክፍል ፫

ኮንሸስ ፓረንቲንግ (conscious parenting = የንቁ-ሕሊና የአስተዳደግ ዘዴ) በአስተውሎት ወይም በmindfulness ላይ የተመሠረተ የልጆች አስተዳደግ ፍልስፍና ሲሆን የሚከተሉትን ዋና-ዋና ባህርያት ያካትታል። * ወላጆች ስለእራሳቸው የተሻለ ግንዛቤ (self-awareness) እንዲኖራቸው እንዲሁም 'እውነተኛ ማንነታቸውን' (authentic self) በበለጠ ለመረዳት ሲሉ ለስሜቶቻቸው ትኩረት እየሰጡ እራሳቸውን ይመረምራሉ (self-reflection) * የልጆችን አስግተዳደግ አስመልክቶ ያሏቸውን

By TW
የአንጀት ደህንነት-ለጠቅላላ ጤንነት

የአንጀት ደህንነት-ለጠቅላላ ጤንነት

በአዕላፋት የሚቆጠሩ የተፈላጊ ረቂቃን ነፍሳት ሕብረተሰብ ወይም ማይክሮባዮም (microbiome) በቆዳችን ላይና በሰውነታችን ውስጥ ይገኛል። ከሌሎቹ የሰውነታችን ክፍሎች ጋር ሲነጻጸር በአንጀታችን ውስጥ የሚገኘው የማይክሮባዮም መጠን ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል። የአንጀት ውስጥ ማይክሮባዮም ማይክሮባዮም እንደ ባክቴሪያ (የbacteria ነጠላ ስም ባክቴሪየም- bacterium ነው)፣ ቫይረሶች (virus/ viruses)፣ ፈንገሶችና (fungus/fungi) ጥገኛ ነፍሳት (parasites) ያሉ ተህዋሳትን

By TW
"ሆዴ ነግሮኝ ነበረ!"

"ሆዴ ነግሮኝ ነበረ!"

"እኔኮ ታውቆኝ ነበረ፣ ሆዴ ነግሮኝ ነበረ፤ ..." ስንል ምን ማለታችን ነው? * ለመረዳትና ለማብራራት በሚያዳግት ሁኔታ አንዳንድ አጋጣሚዎች ወይም ቦታዎች በውስጣችን ያለመመቸት ስሜት የሚቀሰቅሱብን ለምን ይሆን? * ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅነውን ሰው፣ ስለማንነቱ ብዙም ሳንውቅ ሆዳችን እንድንርቀው የሚገፋፋንስ ለምንድን ነው? * ደግሞስ ሆዳችን ነግሮን በእርግጠኝነትና በፍጥነት ትክክለኛ ውሳኔ የምንወስነው እንዴት ሆኖ ነው? የሆድ

By TW