Selam and welcome!

Share
Selam and welcome!
ሰላም (Selam) in Amharic means peace, safety or tranquillity; it also means "hello".

Behind the Fetoon Psychotherapy Blog

This space is dedicated to sharing insights, reflections, and educational materials on mental health and cultural topics relevant to Ethiopian and Eritrean communities. Our posts, written in Amharic, explore the connection between psychological well-being and the unique cultural experiences that shape our communities.

Disclaimer

The content on this blog is intended for informational and entertainment purposes only. While we aim to provide accurate and reliable information, we make no warranties of any kind. We are not responsible for any losses or damages arising from your use of or reliance on this content. You assume full responsibility for how you use the information. Please seek professional advice before making decisions based on anything you read here.

የፍቱን የሥነ-ልቦና አገልግሎት ብሎግ ተልዕኮ

ይህ የተለያዩ አርዕስቶችን እያነሳን አስተያየታችንን የምናካፍልበት እንዲሁም ገንቢ ሃሳቦችንና ውይይቶች የምናበረታታበት የብሎግ ወይም የጦማር መድረክ ነው። ይዘቱ በአብዛኛው የሥነ-አዕምሮና የሥነ-ልቦና ጤናን የሚመለክት ሲሆን በተጨማሪም የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን ኅብረተሰቦችን የሚመለከቱ የማሕበራዊ ኑሮ ጉዳዮችን ያካትታል።

ይህንን በመጫን subscribe ሰብስክራይብ ቢያደርጉ አዳዲስ ጽሑፎችና አስተያየቶች መታከላቸውን የሚያሳውቅ ኢሜይል ይደርስዎታል።

ማሳሰቢያ

የፍቱን የብሎግ/የጦማር መድረክ ላይ የምናካፍላቸው መልዕክቶች የጠቅላላ ዕውቀት መረጃዎችን መሠረት ያደረጉና በተቻለ መጠን የታመኑ ምንጮች ላይ የተመረኮዙ ቢሆኑም ለመዝናኛና ሀሳብ ለመለዋወጫ ታስበው የቀረቡ ናቸው። የጦማሩ ተገልጋዮች ከይዘቱ ጠቃሚ ነገር ሊገበዩ ይችላሉ ብለን ተስፋ ብናደርግም እዚህ የሚያገኟቸውን ሀሳቦች መሠረት በማድረግ ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ሙሉ ኅላፊነት ሊወስዱ ይገባል። በዚያም ሳብያ ለሚደርሱ ዕክሎች፣ ጥፋቶች፣ ወይም ጉዳቶች ዋስትና እንደማንሰጥና ኅላፊነት እንደማንወስድ አጥብቀን እናሳውቃለን። ስለሆነም የጦማሩ ተገልጋዮች እዚህ የሚያግኟቸውን መልዕክቶች መሠረት በማድረግ ውሳኔና እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት የሚመለከተውን ባለሙያ ወይም ፕሮፌሽናል ሰው እንዲያማክሩ እናሳስባለን፡፡


Fetoon - ፍቱን is an Amharic word derived from Geez, an ancient South Semitic language still used in the present day exclusively as liturgical language by the Ethiopian and Eritrean Orthodox Tewahido churches. Fetoon can be translated in English as "tested, capable or effective."

Read more

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፪

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፪

የቤተሰብ መነጣጠል (Disconnection - ዲስኮኔክሽን) በክፍል አንድ የቤተሰብ አባላት በመሀከላቸው በሚኖረው የእርስ በእርስ ጠንካራ መተሳሰር፣ መተባበርና መረዳዳት ላይ ብቻ በማተኮር ለየግል ስሜቶቻቸው ተገቢውን ቦታና ትኩረት ሳይሰጡ በሚቀሩበት ጊዜ፣ እንዲሁም አንዳቸው የሌላኛቸውን ስሜት እንደ የእራሳቸው አድርገው በሚወስዱበት ወቅት መጠማመር ወይም ኢንሜሽመንት ሊከሰት እንደሚችል ለመረዳት ችለናል። አሁን ደግሞ የመነጣጠልን ባህርይ የሚያንጸባርቁ የቤተሰብ አባላት

By TW
የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፩

የቤተሰብ አባላት መጠማመርና መነጣጠል - ክፍል ፩

በ1960ዎቹ (እ.አ.አ.) የቤተሰብ አወቃቀርንና የአባላቱን ግንኙነቶች አስመልክተው ጥናታዊ ሥራዎችን ያበረከቱ ሰው (Salvador Minuchin) የቤተሰብ አባላትን ገደብየለሽ ስሜታዊ የእርስ በእርስ መጠማመር ኢንሜሽመንት (Enmeshment) ብለው ሰይመውታል። በሌላ አነጋገር በቤተሰብ አባላት መሀከል ያለው የቅርበት መጠንና እራስን በእራስ መግዛትና እራስን መቻል ሚዛኑን ካልጠበቅ መጠማመር ሊከሰት ይችላል ማለት ይቻላል። በቤተሰብ አባላት መሀከል ጤናማ

By TW
የግል ገደቦች - Boundaries

የግል ገደቦች - Boundaries

ከሰዎች ጋር በሚኖሩን ግንኙነቶችና መስተጋብሮች ለእራሳችን ገደቦችን (boundaries - ባውንድሪዝ) ማበጀታችን ለህልውናችን መጠበቅና ለሰላማችን አስፈላጊ ሁኔታ ነው። እራስን መገደብ ከ- ለእራስ ገደብን ማበጀት ለየት ይላል።እራስን መገደብ ስሜትን ከመቆጣጠር ጋር የተዛመደ ነው። በአንጻሩ ግን ለእራስ ገደብን ማበጀት ደግሞ በእሤቶቻችን ላይ የተመሠረተ ሲሆን እራስን ከመገንዘብ ጋር የተሳሠረና ለእራሳችን ምን እንደምፈቅድ ወይም እንደማንፈቅድ

By TW
ሳይጠሩሽ አቤት፣ ሳይልኩስሽ ወዴት!

ሳይጠሩሽ አቤት፣ ሳይልኩስሽ ወዴት!

ሰዎች ሳይጠየቁ ምክርን ለሰው የሚለግሱት መልካም በማሰብ ወይም ተመካሪውን ለመደገፍ ቢሆንም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን የሚችልባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች እንዳሉ ማስተዋል ይገባል። የሚከተሉትን አባባሎች እንደ ምሳሌ እንመልከት፦ * "ጸጉርህ ሳሳ - መመልጥ ጀመርክ እንዴ?!" "ታስሮ የተቀለበ በሬ አከልሽ አይደል እንዴ?!" ወዘተ በማለት መልክና አለባበስን እንዲሁም ሰውነትንና ገጽታን አስመልክቶ ተገቢ

By TW